ሀብታም ሲያዳልጠው የሚይዙት እጆች በርካታ ናቸው። ንግግሩ ፍሬቢስ እንኳ ቢሆን ያደንቁለታል፤ ድኃው ሲያዳልጠው ይነቀፋል፤ መልካም ነገር ቢናገም ቦታ የሚሰጠው የለም።
ባለጸጋ ቢናገር ሁሉ ዝም ይላል፤ ቃሉንም ያደንቁለታል፥ ነገሩንም እስከ ደመና ያደርሱለታል፤ ድሃ ግን ምንም በጎ ነገር ቢናገር ይህ ምንድን ነው? ይሉታል፤ ቢሰነካከልም ያዳፉታል።