ከአጠገብህ አታስቁመው፤ ገፍትሮህ ቦታህን ሊይዝ ይችላልና፤ ወንበርህን እንዳይቀማህ በቀኝህ አታስቀምጠው፤ የንግግሬን ትክክለኛነት በመጨረሻ ትገነዘበዋለህ፤ በመጸጸት ቃሎቼን ታስታውሳቸዋለህ።
እንዳይጎዳህ ባጠገብህ አታቁመው፥ በቦታህም አይቀመጥ፤ ሹመትህንም እንዳይወስድብህ በቀኝህ አታስቀምጠው። በመጨረሻም ቃሌን ታውቀው ዘንድ አለህ፥ ምክሬንም ታስበዋለህ።