በኃጢአተኛ ሥራ አትደነቅ፤ በእግዚአብሔር ተማመን፤ በሥራህ ጸንተህ ኑር፤ በድንገት ባንድ አፍታ ድኃውን ማበልጸግ ለእግዚአብሔር ቀላል ነውና።
የኀጢአተኞች ሥራቸው አያስጐምጅህ፥ በእግዚአብሔር እመን፥ ድካምህንም ተስፋ አድርግ፥ ሁሉ በአንድ ጊዜ በእግዚአብሔር ዘንድ ቀሊል ነውና፥ ድሃውንም ድንገት ያከብረዋልና።