ሩት 3:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሚተኛም ጊዜ፥ የሚተኛበትን ስፍራ ተመልከቺ፥ ገብተሽም ከግርጌው በኩል ልብሱን ገልጠሽ በእግሩ አጠገብ ተኚ፤ ምን ማድረግ እንደሚገባሽ እርሱ ራሱ ይነግርሻል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በተኛም ጊዜ፣ የሚተኛበትን ቦታ ልብ ብለሽ እዪና ሄደሽ እግሩን ገልጠሽ ተኚ፤ ከዚያም የምታደርጊውን ራሱ ይነግርሻል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የት እንደሚተኛ ካረጋገጥሽ በኋላ፥ እንቅልፍ ሲወስደው ወደ እርሱ ቀረብ በዪና ከግርጌው በኩል ልብሱን ገልጠሽ በእግሩ አጠገብ ተኚ፤ ምን ማድረግ እንደሚገባሽ እርሱ ራሱ ይነግርሻል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በተኛም ጊዜ የሚተኛበትን ስፍራ ተመልከቺ፥ ገብተሽም እግሩን ግለጪ፥ ተጋደሚም፣ የምታደርጊውንም እርሱ ይነግርሻል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በትኛም ጊዜ የሚተኛበትን ስፍራ ተመልከቺ፤ ገብተሽም እግሩን ግለጪ፤ ተጋደሚም፤ የምታደርጊውንም እርሱ ይነግርሻል።” |
እንግዲህ ሰውነትሽን ታጠቢና ሽቶ ተቀቢ፥ የክት ልብስሽንም ልበሺ፥ ከዚህ በኋላ እርሱ ገብሱን ወደሚወቃበት አውድማ ሂጂ፤ ነገር ግን እስከሚበላና እስከሚጠጣ ድረስ በፊቱ አትታዪ።