የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ሩት 2:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሞዓባዊቱ ሩትም፦ “ደግሞ፥ መከሬን እስኪጨርሱ ድረስ ጐበዛዝቴን ተጠጊ፥ አለኝ” አለቻት።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም ሞዓባዊቷ ሩት፣ “ደግሞም፣ ‘እህሌን ሁሉ ዐጭደው እስኪጨርሱ ድረስ ከሠራተኞቼ አትለዪ!’ ብሎኛል” አለቻት።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ደግሞም ሩት “መከሩን ሰብስበው እስከሚጨርሱ ድረስ ከአጫጆቹ ተጠግተሽ ቈዪ አለኝ” አለቻት።

ምዕራፉን ተመልከት

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሞዓባዊቱ ሩትም፦ ደግሞ፦ መከሬን እስኪጨርሱ ድረስ ጐበዛዝቴን ተጠጊ አለኝ አለቻት።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሞዓባዊቱ ሩትም “ደግሞ ‘መከሬን እስኪጨርሱ ድረስ ጐበዛዝቴን ተጠጊ፤’ አለኝ፤” አለቻት።

ምዕራፉን ተመልከት



ሩት 2:21
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ናዖሚም ምራትዋን፦ “በሕያዋን እና በሙታን ላይ ቸርነቱ የማያልቅበት ጌታ የተባረከ ይሁን” አለቻት። ናዖሚም ደግሞ፦ “ይህ ሰው የቅርብ ዘመዳችን ነው፥ እርሱም ሊቤዡን ከሚችሉት አንዱ ነው” አለቻት።


ናዖሚም ምራትዋን ሩትን፦ “ልጄ ሆይ፥ ከሴት አገልጋዮቹ ጋር ብትወጪ ይሻላል፥ በሌላም እርሻ ባያገኙሽ መልካም ነው” አለቻት።