በዚያ ቀን እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ ብሎ ቃል ኪዳን አደረገ፦ “ከግብጽ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ይህችን ምድር ለዘርህ ሰጥቼአለሁ፥
መዝሙር 80:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጥላዋ ተራሮችን ከደነ፥ ጫፎችዋም እንደ እግዚአብሔር ዝግባ ሆኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቅርንጫፎቿን እስከ ባሕሩ፣ ቍጥቋጦዋንም እስከ ወንዙ ዘረጋች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቅርንጫፎችዋን እስከ ሜዲቴራኒያን ባሕርና እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ዘረጋች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቤ ግን ቃሌን አልሰሙኝም፥ እስራኤልም አላደመጡኝም። |
በዚያ ቀን እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ ብሎ ቃል ኪዳን አደረገ፦ “ከግብጽ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ይህችን ምድር ለዘርህ ሰጥቼአለሁ፥
የሰሎሞንም ግዛት ከኤፍራጥስ ወንዝ ጀምሮ እስከ ፍልስጥኤም ግዛት፥ ከዚያም አልፎ እስከ ግብጽ ወሰን ያለውን አገር ሁሉ ያጠቃልል ነበር፤ የእነዚህም አገሮች ሕዝቦች በጠቅላላ ሰሎሞን በነበረበት ዘመን ሁሉ ለእርሱ ተገዢዎች ሆነው ይገብሩለት ነበር።
ሰሎሞን ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተ ምዕራብ ያለውን ምድር ሁሉ ከቲፍሳሕ ከተማ ጀምሮ እስከ ጋዛ ከተማ ድረስ ይገዛ ነበር፤ ይህም ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተ ምዕራብ የሚገኙትን ነገሥታትን ሁሉ ያጠቃልላል፤ ጐረቤቱ ከሆኑት አገሮችም ሁሉ ጋር በሰላም ይኖር ነበር።
ድንበርህንም ከቀይ ባሕር እስከ ፍልስጥኤም ባሕር፥ ከምድረበዳ እስከ ወንዙ ድረስ አደርጋለሁ፤ በምድሪቱ የሚኖሩትን በእጅህ እጥላለሁና፥ ከፊትህ ታባርራቸዋለህ።