መዝሙር 69:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ ውኃ እስከ ነፍሴ ደርሶብኛልና አድነኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግር መቆሚያ በሌለው፣ በጥልቅ ረግረግ ውስጥ ሰጥሜአለሁ፤ ወደ ጥልቅ ውሃ ገባሁ፤ ሞገዱም አሰጠመኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መቆሚያ ስፍራ ስለ አጣሁ በጥልቅ ረግረግ ውስጥ ለመስረግ ተቃርቤአለሁ፤ በጥልቅ ውሃ ውስጥ እገኛለሁ፤ ውሃ ሙላት ሊያሰጥመኝ ተቃርቦአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነፍሴን የሚሹአት ይፈሩ፥ ይጐስቍሉም፥ ክፉንም የሚመክሩብኝ ወደኋላቸው ይመለሱ፥ ይፈሩም። |
እነሆ፥ በይሁዳ ንጉሥ ቤት የቀሩትን ሴቶች ሁሉ ወደ ባቢሎን ንጉሥ አለቆች ያወጣሉ፤ እነዚያም ሴቶች፦ ‘ባለምዋሎችህ አሳስተውሃል አሸንፈውሃልም፤ አሁን ግን እግሮችህ በጭቃ ውስጥ ገብተዋል እነርሱም ከአንተ ወደ ኋላ ተመልሰዋል’ ይላሉ።
ኤርምያስንም ወሰዱት፤ በእስር ቤቱም አደባባይ ወደነበረው ወደ ንጉሡ ልጅ ወደ መልክያ ጉድጓድ ውስጥ ኤርምያስን በገመድ አውርደው ጣሉት። በጉድጓድም ውስጥ ጭቃ እንጂ ውኃ አልነበረበትም፤ ኤርምያስም ወደ ጭቃው ውስጥ ገባ።