መዝሙር 19:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አገልጋይህ ደግሞ ይጠብቀዋል፥ በመጠበቁም እጅግ ይጠቀማል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስሕተቱን ማን ሊያስተውል ይችላል? ከተሰወረ በደል አንጻኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የራሱን ስሕተት የሚያይ ማንም የለም፤ አምላኬ ሆይ! ከተሰወረ በደል አንጻኝ። |
ጌታም ሙሴን፦ “ወደ እኔ ወደ ተራራው ውጣ፥ በዚያም ሁን፤ እነርሱን እንድታስተምር እኔ የጻፍሁት ሕግና ትእዛዝ ያለበት የድንጋይ ጽላቶች እሰጥሃለሁ” አለው።
ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፥ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ ሁላችንም እንደ ቅጠል ረግፈናል፥ በደላችንም እንደ ነፋስ ወስዶናል።
እኔንም ለመፍራት ሁልጊዜም ትእዛዜን ሁሉ ለመጠበቅ፥ እንዲህ ያለ ልብ ምነው ሁልግዜ በኖራቸው! ለእነርሱ ለልጆቻቸውም ለዘለዓለም መልካም በሆነላቸው ነበር!
በሁለተኛይቱ ግን ሊቀ ካህናት ብቻውን በዓመት አንድ ጊዜ ይገባባታል፤ እርሱም ሰለ ራሱና ስለ ሕዝቡ ኃጢአት የሚያቀርበውን ደም ሳይዝ አይገባም፤
ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ እርስ በእርሳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።