አቤቱ፥ እርሱን ታውቀው ዘንድ ሰው ምንድነው? ታስብለት ዘንድ የሰው ልጅ ምንድነው?
እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህን ያህል በልብህ ስፍራ ትሰጠው ዘንድ ሰው ምንድን ነው? ታስበውስ ዘንድ የሰው ልጅ እስከዚህ ምንድን ነው?
እግዚአብሔር ሆይ! ይህን ያኽል የምትንከባከበው ሰው ምንድን ነው? ይህን ያኽልስ የምታስብለት የሰው ልጅ ምንድን ነው?
እግዚአብሔር ታላቅ ነው፥ ምስጋናውም እጅግ ብዙ ነው፤ ለታላቅነቱም ዳርቻ የለውም።
ከንጹሕ ለመመደብ የሰው ልጅ ምንድነው? ጻድቅስ ለመባል ከሴት የተወለደ ምንድነው?
ሰው ምንድነው ታከብረው ዘንድ፥ ልብህንስ ትጥልበት ዘንድ፥
የጣቶችህን ሥራ ሰማዮችህን ባየሁ ጊዜ፥ ጨረቃንና ከዋክብትን አንተ የሠራሃቸውን፥
ታስበው ዘንድ ሰው ምንድነው? ትጐበኘውም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድነው?
እስትንፋስ አፍንጫው ላይ ባለች በሰው አትታመኑ፤ ከቶ ምን የሚበጅ ነገር አለው!
እንዲያውም በአንድ ስፍራ እንዲህ ተብሎ ተመስክሯል፦ “ታስበው ዘንድ ሰው ምንድነው? ወይስ ትጠነቀቅለት ዘንድ የሰው ልጅ ምንድነው?