ስለ ወንድሞቼ ስለ ባልንጀሮቼም፦ “በውስጥሽ ሰላም ይሁን” ልበል።
ስለ ወንድሞቼና ስለ ባልንጀሮቼ፣ “በውስጥሽ ሰላም ይስፈን” እላለሁ።
በዘመዶቼና በወዳጆቼ ምክንያት ኢየሩሳሌምን “ሰላም ከአንቺ ጋር ይሁን!” እላታለሁ።
እኔ ለሚፈሩህ ሁሉ፥ ትእዛዝህንም ለሚጠብቁ ባልንጀራ ነኝ።
ደስታዬ ሁሉ በምድር ባሉት ቅዱሳንና ክቡራን ላይ ነው።
ዘወትር፦ አምላክህ ወዴት ነው? ሲሉኝ እንባዬ በቀንና በሌሊት ምግብ ሆነኝ።
እንዲህም በሉት፤ ‘ሰላም ለአንተ ይሁን፤ ሰላም ለቤተሰብህና የአንተ ለሆነው ሁሉ ይሁን።