ጥቂት መተኛት፥ ጥቂት ማንቀላፋት፥ ለመተኛት ጥቂት እጅን ማጣጠፍ፥
ጥቂት ማንቀላፋት፤ ጥቂት ማንጐላጀት፤ እጅን አጣጥፎ ጥቂት ጋደም ማለት፤
“ጥቂት እተኛለሁ፤ ጥቂት አንቀላፋለሁ፤ እጄንም አጣጥፌ ለጥቂት ጊዜ ዐርፋለሁ” ስትል፥
ጥቂት ትተኛለህ፥ ጥቂትም ትቀመጣለህ፥ ጥቂት ታሸልባለህ፥ ጥቂትም እጆችህን በደረትህ ታጥፋለህ፤
ሥራ መፍታት እንቅልፍን ታመጣለች፥ የታካችም ነፍስ ትራባለች።
ድሀ እንዳትሆን እንቅልፍን አትውደድ፥ ዓይንህን ክፈት፥ እንጀራም ትጠግባለህ።
ሰካራሞችና ሆዳሞች ይደኸያሉና፥ የእንቅልፍም ብዛት የተቦጫጨቀ ጨርቅ ያስለብሳልና።
አንተ ሰነፍ፥ ወደ ገብረ ጉንዳን ሂድ፥ መንገድዋንም ተመልክተህ ጠቢብ ሁን።
አንተ ሰነፍ፥ እስከ መቼ ትተኛለህ? ከእንቅልፍህስ መቼ ትነሣለህ?
አላዋቂ እጆቹን አጥፎ ይቀመጣል፥ የገዛ ሥጋውንም ይበላል።