ምሳሌ 11:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጻድቃን ምኞት በጎ ብቻ ነው፥ የክፉዎች ተስፋ ግን መቅሠፍት ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጻድቃን ምኞት ምን ጊዜም ፍጻሜው ያማረ ነው፤ የክፉዎች ተስፋ ግን በቍጣ ያከትማል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የደጋግ ሰዎች ምኞት ጥሩ ውጤት አለው፤ የክፉ ሰዎች ምኞት ግን ጥፋትን ያስከትላል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጻድቃን ምኞት መልካም ነው፤ የኃጥኣን ተስፋ ግን ይጠፋል። |
ጌታን አንዲት ነገር ለመንሁት እርሷንም እሻለሁ፥ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በጌታ ቤት እኖር ዘንድ፥ ጌታን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥ መቅደሱንም እመለከት ዘንድ።
ፍርድህን በምድር ላይ በፈረድክ ጊዜ በዓለም የሚኖሩ ጽድቅን ይማራሉና ነፍሴ በሌሊት ትናፍቅሃለች፥ መንፈሴም በውስጤ ወደ አንተ ትገሠግሣለች።