ዘኍል 6:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አውራውንም በግ ለአንድነት መሥዋዕት ከሌማቱ እርሾ ካልገባበት እንጀራ ጋር ወደ ጌታ ያቀርባል፤ ካህኑም ደግሞ የእህሉን ቁርባንና የመጠጡን ቁርባን ያቀርባል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመሶብ ያለውን ቂጣ፣ እንዲሁም አውራ በጉን የኅብረት መሥዋዕት አድርጎ ከእህሉና ከመጠጡ ቍርባን ጋራ ካህኑ ለእግዚአብሔር ያቅርብ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አውራውን በግ የአንድነት መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ያቀርበዋል፤ እርሱንም በመሶብ ካለው እንጀራ ጋር ያቀርበዋል፤ ቀጥሎም የእህሉን ቊርባንና የመጠጡን መባ ያቀርባል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አውራውንም በግ ለደኅንነት መሥዋዕት ከሌማቱ ቂጣ እንጀራ ጋር ወደ እግዚአብሔር ያቀርባል፤ ካህኑም ደግሞ የእህሉን ቍርባንና የመጠጡን ቍርባን ያቀርባል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አውራውንም በግ ለደኅንነት መሥዋዕት ከሌማቱ ቂጣ እንጀራ ጋር ወደ እግዚአብሔር ያቀርባል፤ ካህኑም ደግሞ የእህሉን ቍርባንና የመጠጡን ቍርባን ያቀርባል። |
ናዝራዊውም የተቀደሰውን የራሱን ጠጉር በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ይላጫል፥ የተቀደሰውንም ራስ ጠጉር ወስዶ ከአንድነት መሥዋዕት በታች ወዳለው እሳት ይጥለዋል።