ዘኍል 5:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰውዮውም ከበደል ንጹሕ ይሆናል፥ ሴቲቱም በደልዋን ትሸከማለች።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባልየውም ከበደል ንጹሕ ይሆናል፤ ሴትዮዋ ግን በበደሏ ምክንያት የሚመጣውን ፍዳ ትቀበላለች።’ ” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባልየውም ከበደል ነጻ ይሆናል፤ ሴትዮዋ ያመነዘረች ሆና ከተገኘች ግን በበደልዋ ምክንያት የሚመጣባትን ፍዳ ትቀበላለች።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህኑም ይህን ሕግ ሁሉ ያደርግባታል። ሰውየውም ከኀጢአት ንጹሕ ይሆናል፤ ሴቲቱም ኀጢአቷን ትሸከማለች።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰውዮውም ከኃጢአት ንጹሕ ይሆናል፥ ሴቲቱም ኃጢአትዋን ትሸከማለች። |
ወይም በባልዋ ላይ የቅንዓት መንፈስ መጥቶበት ስለ ሚስቱ በሚቀና ጊዜ ቅንዓትን በሚመለከት ሕጉ ይህ ነው፤ ሴቲቱንም በጌታ ፊት ያቁማት፥ ካህኑም ይህን ሕግ ሁሉ በእርሷ ላይ ይፈጽምባት።
ነገር ግን ንጹሕ የሆነ ሰው በመንገድም ላይ ያልሆነ የፋሲካን በዓል ባያከብር፥ ያ ሰው ከሕዝቡ ዘንድ ተለይቶ ይጠፋል፤ የጌታን ቁርባን በተወሰነለት ጊዜ አላቀረበምና ያ ሰው ኃጢአቱን ይሸከማል።