ዘኍል 5:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን በባልሽም ሥልጣን ሥር እያለሽ እርሱን ትተሽ ፈቀቅ በማለት ራስሽን ያረከስሽ እንደሆነ፥ ከባልሽም ሌላ ከወንድ ጋር ተኝተሽ እንደሆነ፤’ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን በትዳር ላይ እያለሽ ወደ ርኩሰት በማዘንበል ከባልሽ ሌላ ከወንድ ጋራ በመተኛት ከጐደፍሽ”፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ከባልሽ ጋር እያለሽ ከሌላ ወንድ ጋር በመተኛት ራስሽን ያረከስሽ ከሆነ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ባልሽን ትተሽ ረክሰሽ እንደ ሆነ፥ ከባልሽም ሌላ ወንድ ከአንቺ ጋር ተኝቶ እንደ ሆነ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ባልሽን ትተሽ ረክሰሽ እንደ ሆነ፥ ከባልሽም ሌላ ከወንድ ጋር ተኝተሽ እንደሆነ፤ |