የማንሣት ቁርባን ነውና ከእስራኤል ልጆች ዘንድ የአሮንና የልጆቹ ድርሻ ይሁን፤ የእስራኤል ልጆች የሚያቀርቡት የሰላም መሥዋዕታቸው የማንሣት ቁርባን ይሆናል፤ ለጌታ የማንሣት ቁርባን ይሆናል።
ዘኍል 5:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የማናቸውም ሰው የተቀደሱ ነገረሮች ለራሱ ለሰውዬው ይሆናሉ፤ ማናቸውም ሰው ለካህኑ የሚሰጠው ሁሉ ግን ለካህኑ ይሆናል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእያንዳንዱ ሰው የተቀደሰ ስጦታ ለካህኑ ይሆናል፤ ለካህኑ የሚሰጠውም ሁሉ የራሱ ይሆናል።’ ” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እያንዳንዱ ሰው ለእግዚአብሔር የሚያቀርበው ልዩ ስጦታ የራሱ የሰውዬው ነው፤ ለካህኑ ከሰጠ ግን የካህኑ ይሆናል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተቀደሰ የሰው ነገር ሁሉ፥ ሰውም ለካህኑ የሚሰጠው ሁሉ ለእርሱ ይሁን።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተቀደሰ የሰው ነገር ሁሉ፥ ሰውም ለካህኑ የሚሰጠው ሁሉ ለእርሱ ይሁን። |
የማንሣት ቁርባን ነውና ከእስራኤል ልጆች ዘንድ የአሮንና የልጆቹ ድርሻ ይሁን፤ የእስራኤል ልጆች የሚያቀርቡት የሰላም መሥዋዕታቸው የማንሣት ቁርባን ይሆናል፤ ለጌታ የማንሣት ቁርባን ይሆናል።
ለጌታም ከሆነው በእሳት ከሚቀርበው ቁርባን ለአንተም ለልጆችህም የተሰጠ ድርሻ ነውና በቅዱስ ስፍራ ትበሉታላችሁ፤ ይህንንም እንዲህ ታዝዣለሁና።