“የሰለጰዓድ ልጆች ትክክለኛ ነገር ተናግረዋል፤ በአባታቸው ወንድሞች መካከል የርስት ድርሻ ስጣቸው፤ የአባታቸውን ርስት ወደ እነርሱ ይተላለፍ።
ዘኍል 36:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም የእስራኤልን ልጆች እንደ ጌታ ቃል እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፦ “የዮሴፍ ልጆች ነገድ እውነት የሆነን ነገር ተናግረዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ ሙሴ እግዚአብሔር በተናገረው መሠረት እስራኤላውያንን እንዲህ ሲል አዘዛቸው፤ “የዮሴፍ ነገድ የተናገረው ትክክል ነው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሙሴ ለእስራኤል ሕዝብ ከእግዚአብሔር የተቀበለውን ትእዛዝ እንዲህ ሲል አስተላለፈ፤ “የምናሴ ነገድ የተናገሩት ሁሉ ትክክል ነው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም የእስራኤልን ልጆች እንደ እግዚአብሔር ቃል እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፥ “የዮሴፍ ልጆች ነገድ በእውነት ተናገሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም የእስራኤልን ልጆች እንደ እግዚአብሔር ቃል እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፦ የዮሴፍ ልጆች ነገድ በእውነት ተናገሩ። |
“የሰለጰዓድ ልጆች ትክክለኛ ነገር ተናግረዋል፤ በአባታቸው ወንድሞች መካከል የርስት ድርሻ ስጣቸው፤ የአባታቸውን ርስት ወደ እነርሱ ይተላለፍ።
ለእስራኤልም ልጆች ኢዮቤልዩ በመጣ ጊዜ ርስታቸው እነርሱ ወደ አሉበት ነገድ ርስት ይጨመራል፤ ርስታቸውም ከአባቶቻችን ነገድ ርስት ይወሰዳል።”
“በተናገራችሁኝም ጊዜ ጌታ የእናንተን ቃል ጽምፅ ሰማ፤ ጌታም አለኝ፦ ‘የዚህን ሕዝብ ነገር፥ የተናገሩህን ቃል ድምፅ ሰምቼአለሁ፤ የተናገሩህ ሁሉ መልካም ነው።