ድንበሩ ከባሕሩ ጀምሮ እስከ የደማስቆ ድንበር ሰሜን የሆነው ሐጻርዔኖን ይሆናል፥ በሰሜንም በኩል የሐማት ድንበር አለ። ይህም የሰሜኑ ድንበር ነው።
ዘኍል 34:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድንበሩም ወደ ዚፍሮን ይዘረጋል መጨረሻውም ሐጸርዔናን ይሆናል፤ ይህ የሰሜን ድንበራችሁ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስከ ዚፍሮን በመቀጠል መጨረሻው ሐጻርዔናን ይሆናል፤ በሰሜን በኩል ያለው ወሰናችሁ ይኸው ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ዚፍሮን ከተሻገረም በኋላ በሐጻርዔናን ይቆማል፤ ይህም የሰሜን ድንበራችሁ ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳርቻውም ወደ ዲፍሮና ያልፋል፤ መውጫውም አርሴናይን ይሆናል፤ በመስዕ በኩል ያለው ወሰናችሁም በዚህ ይሁናችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳርቻውም ወደ ዚፍሮን ያልፋል እስከ ሐጸርዔናንም ድረስ ይወጣል፤ ይህ የሰሜን ዳርቻችሁ ይሆናል። |
ድንበሩ ከባሕሩ ጀምሮ እስከ የደማስቆ ድንበር ሰሜን የሆነው ሐጻርዔኖን ይሆናል፥ በሰሜንም በኩል የሐማት ድንበር አለ። ይህም የሰሜኑ ድንበር ነው።
የነገዶቹ ስም ይህ ነው። ከሰሜን ወሰን በሔትሎን መንገድ አጠገብ ወደ ሐማት መግቢያ በደማስቆም ድንበር ባለው በሐጸርዔናን በሐማትም አጠገብ በሰሜን በኩል ካለው ከሰሜን ድንበር ይጀምራል። ወርዳቸውም ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ይሆናል። ለዳን አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል።