ከእስራኤል ልጆች ርስት ለሌዋውያን የምትሰጡአቸውን ከተሞች እንዲሁ ስጡ፤ ከብዙዎቹ ብዙ፥ ከጥቂቶቹ ጥቂት ትወስዳላችሁ፤ እያንዳንዱ እንደ ወረሱት እንደ ርስታቸው መጠን ከከተሞቻቸው ለሌዋውያን ይሰጣሉ።”
ዘኍል 33:54 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድሪቱንም በየወገኖቻችሁ በዕጣ ትወርሳላችሁ፤ ለብዙዎች እንደ ብዛታቸው ለጥቂቶቹም እንደ ጥቂትነታቸው መጠን ርስትን ትሰጣላችሁ፤ እያንዳንዱ ሁሉ ዕጣው እንደ ወጣለት በዚያ ርስቱ ይሆናል፤ በየአባቶቻችሁ ነገዶች ትወርሳላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድሪቱንም በየጐሣዎቻችሁ በዕጣ ተከፋፈሉ። ከፍ ያለ ቍጥር ላለው ሰፋ ያለውን፣ ዝቅተኛ ቍጥር ላለው ደግሞ አነስተኛውን ስጡ፤ ምንም ይሁን ምን በዕጣ የወጣላቸው፣ የየራሳቸው ርስት ይሆናል። አከፋፈሉም በየአባቶቻችሁ ነገዶች አንጻር ይሁን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምድሪቱንም በተለያዩት ነገዶችና ጐሣዎች መካከል በዕጣ ተከፋፈሉ፤ የጐሣው ቊጥር ከፍ ላለው ሰፊ መሬት ይሰጠው፤ የጐሣው ቊጥር አነስተኛ ለሆነው ደግሞ ጠበብ ያለ መሬት ይሰጠው። እያንዳንዱ ሁሉ ዕጣው እንደ ወጣለት በዚያ ርስቱ ይሆናል፤ በየአባቶቻችሁ ነገዶች ምድሪቱን በርስትነት ትረከባላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምድሪቱንም ትወርሳላችሁ፤ በየወገኖቻችሁም ትከፋፈሏታላችሁ፤ ለብዙዎች ድርሻቸውን አብዙላቸው፤ ለጥቂቶችም ድርሻቸውን ጥቂት አድርጉ፤ እያንዳንዱ ሁሉ ዕጣ እንደ ወደቀለት በዚያ ርስቱ ይሆናል፤ በየአባቶቻችሁ ነገዶች ትወርሳላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምድሪቱንም በየወገኖቻችሁ በዕጣ ትወርሳላችሁ፤ ለብዙዎች እንደ ብዛታቸው ለጥቂቶቹም እንደ ጥቂትነታቸው መጠን ርስትን ትሰጣላችሁ፤ እያዳንዱ ሁሉ ዕጣ እንደ ወደቀለት በዚያ ርስቱ ይሆናል፤ በየአባቶቻችሁ ነገዶች ትወርሳላችሁ። |
ከእስራኤል ልጆች ርስት ለሌዋውያን የምትሰጡአቸውን ከተሞች እንዲሁ ስጡ፤ ከብዙዎቹ ብዙ፥ ከጥቂቶቹ ጥቂት ትወስዳላችሁ፤ እያንዳንዱ እንደ ወረሱት እንደ ርስታቸው መጠን ከከተሞቻቸው ለሌዋውያን ይሰጣሉ።”
በተራራማውም አገር የሚኖሩትን ሁሉ ከሊባኖስ ጀምሮ እስከ ማሴሮን ድረስ ሲዶናውያን ሁሉ፥ እኔ ራሴ እነዚህን ከእስራኤል ልጆች ፊት አባርራቸዋለሁ፤ እንዳዘዝሁህም ምድራቸውን ለእስራኤል ብቻ ርስት አድርገህ አካፍላቸው።