ዘኍል 32:39 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምናሴም ልጅ የማኪር ልጆች ወደ ገለዓድ ሄዱ፥ ያዝዋትም፥ በእርሷም የነበሩትን አሞራውያንን አሳደዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምናሴ ልጅ የሆነው የማኪር ዘሮች ወደ ገለዓድ ሄደው ምድሪቱን በመያዝ፣ እዚያ የነበሩትን አሞራውያን አሳደዷቸው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምናሴ ልጅ የማኪር ቤተሰብ የገለዓድን ምድር በመውረር ወረሰ፤ በዚያም ይኖሩ የነበሩትን አሞራውያንን አባረረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምናሴም ልጅ የማኪር ልጅ ወደ ገለዓድ ሄዶ ገለዓድን ያዘ፤ በእርስዋም የነበሩትን አሞሬዎናውያንን አጠፋ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የምናሴም ልጅ የማኪር ልጆች ወደ ገለዓድ ሄዱ፥ ወሰዱአትም፥ በእርስዋም የነበሩትን አሞራውያንን አሳደዱ። |
ለምናሴ ነገድ ዕጣው ይህ ነው፤ የዮሴፍ በኩር እርሱ ነውና። የምናሴም በኩር የገለዓድ አባት ማኪር ብርቱ ተዋጊ ስለ ነበረ ገለዓድንና ባሳንን ወረሰ።
በዚያም ዓመት የእስራኤልን ልጆች ሥቃይ አበዙባቸው፥ በዮርዳኖስ ማዶ በአሞራውያን አገር በገለዓድ ውስጥ ያሉትን የእስራኤልን ልጆች ሁሉ ዐሥራ ስምንት ዓመት ተጋፉአቸው።
በአማሌቅ ዘንድ ሥር የነበራቸው እነርሱ ከኤፍሬም፥ ብንያም ሆይ፥ በሕዝብህ መካከል ከአንተ በኋላ ወረዱ፥ አለቆች ከማኪር፥ የንጉሥንም ዘንግ የሚይዙ ከዛብሎን ወረዱ።