ዘኍል 32:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም ቀን የጌታ ቁጣ ነደደ እንዲህም ብሎ ማለ፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያም ቀን የእግዚአብሔር ቍጣ ነደደ፤ እንዲህም ሲል ማለ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ቀን እግዚአብሔር እጅግ ተቈጥቶ እንዲህ አለ፤ ‘በእኔ በመተማመን ስላልጸኑ፥ ከግብጽ ምድር ከወጡት ዕድሜአቸው ኻያ ዓመት የሞላቸውና ከዚያም በላይ የሆኑ ሁሉ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ልሰጣቸው ቃል ወደገባሁላቸው ምድር ከቶ እንደማይገቡ ምዬአለሁ።’ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን እግዚአብሔር ተቈጣ፤ እንዲህም ብሎ ማለ፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ቀን የእግዚአብሔር ቁጣ ነደደ፥ |
ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ይህ ሕዝብ እስከ መቼ ይንቀኛል? በመካከላቸውም ስላደረግሁት ተአምራት ሁሉ እንኳ እስከ መቼ ድረስ በእኔ አያምኑም?
በድኖቻችሁ በዚህ ምድረ በዳ ይወድቃሉ፤ ከአጠቃላይም ቁጥራችሁ፥ በእኔ ላይ ያጉረመረሙ ዕድሜአቸው ሀያ ዓመት የሆናቸውና ከዚያም በላይ ሆነው የተቈጠሩት ሁሉ፥