ዘኍል 31:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ሙሴን እንዳዘዘ ከምድያም ጋር ተዋጉ፥ ወንዶችንም ሁሉ ገደሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ከምድያም ጋራ ተዋጉ፤ ወንዱንም በሙሉ ፈጁት፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት በምድያማውያን ላይ አደጋ ጥለው ወንዶቹን በሙሉ ገደሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘ ከምድያም ጋር ተዋጉ፤ ወንዶችንም ሁሉ ገደሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘ ከምድያም ጋር ተዋጉ፥ ወንዶችንም ሁሉ ገደሉ። |
በዚህ ጊዜ ምድያማውያን ሁሉ፥ አማሌቃውያንና ሌሎች የምሥራቅ ሕዝቦች ያላቸውን አስተባብረው የዮርዳኖስን ወንዝ በመሻገር በኢይዝራኤል ሸለቆ ሰፈሩ።
ዳዊትም ምድሪቱን በመታበት ጊዜ፥ ወንድም ሆነ ሴት በሕይወት አላስቀረም፤ በጎችንና ላሞችን፥ አህዮችንና ግመሎችን እንዲሁም ልብሶችን ወሰደ፤ ወደ አኪሽም ይዞ ተመለሰ።