ዘኍል 31:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከብዙ ሺህ እስራኤላውያን መካከል ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከየነገዱ አንድ አንድ ሺህ፥ ለጦርነት የተዘጋጁ ሰዎች ተመለመሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ከእስራኤል ጐሣዎች ተወጣጥቶ ከእያንዳንዱ ነገድ አንድ ሺሕ፣ በአጠቃላይ ዐሥራ ሁለት ሺሕ ሰው ለጦርነት ተዘጋጀ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ከብዙ ሺህ እስራኤላውያን መካከል ከያንዳንዱ ነገድ አንዳንድ ሺህ ተውጣጥቶ ዐሥራ ሁለት ሺህ የታጠቀ ሠራዊት ለጦርነት ተዘጋጀ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእስራኤልም አእላፋት፥ ከየነገዱ አንድ አንድ ሺህ ቈጠሩ፤ ለጦርነት የተሰለፉትም ዐሥራ ሁለት ሺህ ሆኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእስራኤልም አእላፋት አሥራ ሁለት ሺህ፥ ከየነገዱ አንድ አንድ ሺህ፥ ለጦርነት የተሰለፉ ሰዎች ተሰጡ። |
ሙሴም ከየነገዱ አንድ አንድ ሺህ ወደ ጦርነት ላከ፤ እነርሱንና የካህኑን የአልዓዛርን ልጅ ፊንሐስን ወደ ጦርነት ላካቸው፤ የመቅደሱንም ዕቃ የሚነፋውንም የማስጠንቀቂያ መለከት በእጁ ሰጠው።