ለሴቲቱም አላት፥ “በእርግዝናሽ ወራት ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፥ በጭንቅ ትወልጃለሽ፥ ይህም ሁሉ ሆኖ ፍላጎትሽ ለባልሽ ይሆናል፥ እርሱም ገዥሽ ይሆናል።”
ዘኍል 30:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባልዋ ግን በሰማበት ቀን ቢከለክላት፥ በእርሷ ላይ ያለውን ስእለትዋን ከአንደበትዋም በችኮላ ተናግራ ራስዋን በመሐላ ያሰረችበትን ነገር ከንቱ ያደርገዋል፤ ጌታም ይቅር ይላታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሆኖም ባሏ ይህንኑ ሰምቶ ከከለከላት ግን ለመፈጸም የተሳለችውንም ሆነ አምልጧት ተናግራ ራሷን ግዴታ ውስጥ ያስገባችበትን ነገር ስለሚያስቀር እግዚአብሔር ከዚህ ነጻ ያደርጋታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባልዋ ስለ ጉዳዩ ሰምቶ ከከለከላት ግን የመፈጸም ግዴታ የለባትም፤ ስእለትዋን ለመፈጸም ያልቻለችው ባልዋ ስለ ከለከላት በመሆኑ እግዚአብሔር ይቅርታ ያደርግላታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባልዋ ግን በሰማበት ቀን ቢከለክላት፥ ስእለቷና ራስዋን ያሰረችበት መሐላ አይጸኑም፤ ባልዋ ከልክሎአታልና፤ እግዚአብሔርም ይቅር ይላታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባልዋ ግን በሰማበት ቀን ቢከለክላት፥ በእርስዋ ላይ ያለውን ስእለትዋን ራስዋንም በመሐላ ያሰረችበትን የአፍዋን ነገር ከንቱ ያደርገዋል፤ እግዚአብሔርም ይቅር ይላታል። |
ለሴቲቱም አላት፥ “በእርግዝናሽ ወራት ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፥ በጭንቅ ትወልጃለሽ፥ ይህም ሁሉ ሆኖ ፍላጎትሽ ለባልሽ ይሆናል፥ እርሱም ገዥሽ ይሆናል።”
እኛስ ለሰማይ ንግሥት ባጠንንላት የመጠጥንም ቁርባን ባፈሰስንላት ጊዜ፥ በውኑ ያለ ባሎቻችን ፈቃድ ምስልዋ ያለበት እንጐቻ አድርገንላታልን? የመጠጥንስ ቁርባን አፍስሰንላታልን?”
ማናቸውም ሰው ክፉን ወይም መልካምን ለማድረግ ሳያስብ በከንፈሩ ተናግሮ ቢምል፤ ሳያስብ የማለው ስለ ማናቸውም ነገር ቢሆን፤ ይህንንም ሳይታወቀው ቢያደርግ፤ በታወቀው ጊዜ ከዚህ ነገር በአንዱ በደለኛ ይሆናል።
ሚስት በገዛ ሰውነቷ ላይ ሥልጣን የላትም፤ ሥልጣን ለባሏ ነው እንጂ፤ እንዲሁም ደግሞ ባል በገዛ ሰውነቱ ላይ ሥልጣን የለውም፤ ሥልጣን ለሚስቱ ነው እንጂ።
ባሏ ሕልቃናም፥ “መልካም መስሎ የታየሽን አድርጊ፤ ጡት እስክታስጥይው ድረስ እዚሁ ቆይ፤ ብቻ ጌታ ቃሉን ያጽናልሽ” አላት። ስለዚህ ሴቲቱ ሕፃኑን ጡት እስክታስጥለው ድረስ እያጠባችው በቤቷ ተቀመጠች።