ዘኍል 28:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በመጀመሪያው ወር ከወሩም በዓሥራ አራተኛው ቀን የጌታ ፋሲካ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥራ አራተኛው ቀን የእግዚአብሔር ፋሲካ በዓል ይከበራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የጌታ የፋሲካ በዓል የሚከበረው የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥራ አራተኛው ቀን ይሁን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በመጀመሪያው ወር ከወሩም በዐሥራ አራተኛው ቀን የእግዚአብሔር ፋሲካ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመጀመሪያው ወር ከወሩም በአሥራ አራተኛው ቀን የእግዚአብሔር ፋሲካ ነው። |
የቂጣውን በዓል ጠብቅ፤ በተመደበው በአቢብ ወር ሰባት ቀን ያልቦካ ቂጣ እንዳዘዝሁህ ትበላለህ፤ በዚህ ወር ከግብጽ ምድር ወጥታችኋልና፥ በፊቴም ባዶ እጃችሁን አትታዩ።