ከዚያም ይሁዳ ምራቱን ትዕማርን፥ “ልጄ ሴሎም ለአካለ መጠን እስኪደርስ ድረስ ወደ አባትሽ ቤት ሄደሽ መበለት ሆነሽ ብትኖሪ ይሻላል” አላት፤ ይህን ያለውም፥ ሴሎም እንደ ወንድሞቹ ተቀሥፎ ይሞትብኛል ብሎ ስለ ሠጋ ነበር። ትዕማርም እንዳላት ሄደች፤ በአባቷም ቤት ተቀመጠች።
ዘኍል 26:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በየወገናቸው የይሁዳም ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ከሴሎም የሴሎማውያን ወገን፥ ከፋሬስ የፋሬሳውያን ወገን፥ ከዛራ የዛራውያን ወገን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የይሁዳ ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ በሴሎም በኩል፣ የሴሎማውያን ጐሣ፤ በፋሬስ በኩል፣ የፋሬሳውያን ጐሣ፤ በዛራ በኩል፣ የዛራውያን ጐሣ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቀሩት የይሁዳ ልጆች ሴሎም ፋሬስ ዛራና ተወላጆቻቸው ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከያሱብ የያሱባውያን ወገን፥ ከሥምራ የሥምራውያን ወገን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የይሁዳም ልጆች በየወገናቸው፤ ከሴሎም የሴሎማውያን ወገን፥ ከፋሬስ የፋሬሳውያን ወገን፥ ከዛራ የዛራውያን ወገን። |
ከዚያም ይሁዳ ምራቱን ትዕማርን፥ “ልጄ ሴሎም ለአካለ መጠን እስኪደርስ ድረስ ወደ አባትሽ ቤት ሄደሽ መበለት ሆነሽ ብትኖሪ ይሻላል” አላት፤ ይህን ያለውም፥ ሴሎም እንደ ወንድሞቹ ተቀሥፎ ይሞትብኛል ብሎ ስለ ሠጋ ነበር። ትዕማርም እንዳላት ሄደች፤ በአባቷም ቤት ተቀመጠች።
የመበለትነት ልብሷን አውልቃ፥ ማንነቷ እንዳይታወቅ ፊቷን በሻሽ ተከናንባ ወደ ተምና በሚወስደው መንገድ ዳር ባለች ኤናይም በተባለች ከተማ መግቢያ ላይ ተቀመጠች፤ ይህን ያደረገችው፥ ሴሎም ለአካለ መጠን ቢደርስም፥ እርሷን እንዲያገባ አባቱ አለመፈለጉን ስላወቀች ነው።
ከይሁዳ ልጆችና ከብንያም ልጆች የተወሰኑት በኢየሩሳሌም ተቀመጡ። ከይሁዳ ልጆች፦ ከፋሬስ ልጆች የማሃላልኤል ልጅ፥ የሽፋጥያ ልጅ፥ የአማርያ ልጅ፥ የዘካርያስ ልጅ፥ የዑዚያ ልጅ ዓታያ፤