ዘኍል 26:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ዕድሜው ሀያ ዓመት የሆነውንና ከዚያም በላይ ያለውን፥ በእስራኤል ወደ ጦርነት የሚወጣውን ሁሉ፥ የእስራኤልን ልጆች ማኅበር ሁሉ በየአባቶቻቸው ቤት ቁጠሩ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸውን፣ በእስራኤልም ጦር ሰራዊት ውስጥ ለማገልገል ብቃት ያላቸውን ሁሉ ከመላው የእስራኤል ማኅበረ ሰብ ከየቤተ ሰቡ ቍጠሩ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በመላው የእስራኤል ማኅበር በየቤተሰቡ ዕድሜአቸው ኻያ ዓመት የሞላቸውንና ከዚያም በላይ የሆኑትን፥ ወታደር ሆነው ለማገልገል ብቃት ያላቸውን ወንዶች ልጆች ሁሉ ቊጠሩ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለውን፥ ከእስራኤል ወደ ሰልፍ የሚወጣውን ሁሉ፥ የእስራኤልን ልጆች ማኅበር ሁሉ በየአባቶቻቸው ቤት ቍጠሩ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሀያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለውን፥ በእስራኤል ወደ ሰልፍ የሚወጣውን ሁሉ፥ የእስራኤልን ልጆች ማኅበር ሁሉ በየአባቶቻቸው ቤት ቍጠሩ ብሎ ተናገራቸው። |