ዘኍል 22:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም ወደ በለዓም መጥቶ፦ “እነዚህ ከአንተ ጋር ያሉት ሰዎች እነማን ናቸው?” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም ወደ በለዓም መጥቶ፣ “ከአንተ ጋራ ያሉት እነዚህ ሰዎች እነማን ናቸው?” ሲል ጠየቀው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም ወደ በለዓም መጥቶ “እነዚህ ከአንተ ጋር ያሉት ሰዎች እነማን ናቸው?” ሲል ጠየቀው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ወደ በለዓም መጥቶ፥ “እነዚህ በአንተ ዘንድ ያሉ ሰዎች እነማን ናቸው?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ወደ በለዓም መጥቶ፦ እነዚህ በአንተ ዘንድ ያሉ ሰዎች እነማን ናቸው? አለው። |
ዮሴፍም ለፈርዖን እንዲህ አለው፤ “ሁለቱም የፈርዖን ሕልሞች ተመሳሳይና አንድ ዓይነት ናቸው፤ እግዚአብሔር ወደ ፊት የሚያደርገውን ለፈርዖን ገልጦለታል።
እግዚአብሔርም ወደ በለዓም በሌሊት መጥቶ እንዲህ አለው፦ “ሰዎቹ ሊጠሩህ መጥተው እንደሆነ፥ ተነሣ ከእነርሱም ጋር ሂድ፤ ነገር ግን የምነግርህን ቃል ብቻ ታደርጋለህ።”
በዚያ ቀን ብዙዎች ‘ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ! በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን? በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን? በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን?’ ይሉኛል።