ዘኍል 22:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም እንዲህ አላቸው፦ “ዛሬ ሌሊት በዚህ እደሩ፥ ጌታም እንደሚነግረኝ እመልስላችኋለሁ”፤ የሞዓብም አለቆች በበለዓም ዘንድ ተቀመጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በለዓምም፣ “እግዚአብሔር የሚሰጠኝን መልስ አመጣላችኋለሁና የዛሬን ሌሊት እዚሁ ዕደሩ” አላቸው። ስለዚህም የሞዓብ አለቆች ከርሱ ዘንድ ቈዩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በለዓምም “እዚሁ ዕደሩና ነገ ጧት እግዚአብሔር የሚነግረኝን ሁሉ እነግራችኋለሁ” አላቸው፤ በዚህ ዐይነት የሞአባውያን መሪዎች ከበለዓም ጋር ቈዩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፥ “ዛሬ ሌሊት በዚህ እደሩ፤ እግዚእብሔርም የሚነግረኝን እነግራችኋለሁ” አላቸው፤ የሞዓብ አለቆችም በበለዓም ዘንድ አደሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ ዛሬ ሌሊት በዚህ እደሩ፥ እግዚአብሔርም እንደሚነግረኝ እመልስላችኋለሁ አላቸው፤ የሞዓብም አለቆች በበለዓም ዘንድ ተቀመጡ። |
ሕዝብ እንደሚመጣ ወደ አንተ ይመጣሉ፥ እንደ ሕዝቤም በፊትህ ይቀመጣሉ፥ ቃልህንም ይሰማሉ ነገር ግን አያደርጉትም፤ በአፋቸው ብዙ ፍቅር ይገልጣሉ፥ ልባቸው ግን ያልተገባ ጥቅማቸውን ይከተላልና።
በለዓምም መልሶ የባላቅን ባርያዎች እንዲህ አላቸው፦ “ባላቅ በቤቱ የሞላውን ወርቅና ብር ቢሰጠኝ፥ ትንሹን ወይም ትልቁን ነገር በመፈጸም የአምላኬን የጌታን ቃል ለመተላለፍ አልችልም፤
በለዓምም ባላቅን እንዲህ አለው፦ “እነሆ፥ ወደ አንተ መጥቼአለሁ፤ በውኑ እኔ አሁን አንዳችን ነገር ለመናገር እችላለሁን? እግዚአብሔር በአፌ የሚያድርገውን ቃል እርሱን እናገራለሁ።”
የሞዓብ ሽማግሌዎችና የምድያም ሽማግሌዎችም ለምዋርቱ የሚከፈለውን ገንዘብ በእጃቸው ይዘው ሄዱ፤ ወደ በለዓምም መጡ፥ የባላቅንም ቃላት ነገሩት።
በለዓምም ባላቅን እንዲህ አለው፦ “በሚቃጠል መሥዋዕትህ ዘንድ ቆይ፥ እኔም እሄዳለሁ፤ ምናልባት ጌታ ሊያገኘኝ ይመጣል፤ እርሱም የሚገልጥልኝን እነግርሃለሁ።” ከዚያም እርሱ ወደ ኮረብታው ሄደ።
‘ባላቅ በቤቱ የሞላውን ብርና ወርቅ ቢሰጠኝ፥ በራሴ ፈቃድ መልካምን ወይም ክፉን ነገር ለማድረግ የጌታን ቃል መተላለፍ አልችልም፤ ጌታ የተናገረውን እርሱን እናገራለሁ።’