ገዥዎችሽ ዐመፀኞችና የሌባ ግብረ ዐበሮች ናቸው፤ ሁሉም ጉቦን ይወዳሉ፤ እጅ መንሻንም በብርቱ ይፈልጋሉ፤ አባት ለሌላቸው አይቆሙም፤ የመበለቶችንም አቤቱታ አይሰሙም።
ዘኍል 22:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሞዓብ ሽማግሌዎችና የምድያም ሽማግሌዎችም ለምዋርቱ የሚከፈለውን ገንዘብ በእጃቸው ይዘው ሄዱ፤ ወደ በለዓምም መጡ፥ የባላቅንም ቃላት ነገሩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሞዓብና የምድያም ሽማግሌዎችም ለሟርት የሚከፈለውን ዋጋ ይዘው ሄዱ፤ በለዓም ዘንድ በደረሱ ጊዜም የባላቅን መልእክት ነገሩት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ የሞአባውያንና የምድያማውያን ሽማግሌዎች ስለ ርግማን የሚከፈለውን ገንዘብ ይዘው ወደ በለዓም በመሄድ የባላቅን መልእክት ሰጡት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሞዓብ ሽማግሌዎችና የምድያም ሽማግሌዎችም የምዋርቱን ዋጋ በእጃቸው ይዘው ሄዱ፤ ወደ በለዓምም መጡ፤ የባላቅንም ቃል ነገሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሞዓብ ሽማግሌዎችና የምድያም ሽማግሌዎችም የምዋርቱን ዋጋ በእጃቸው ይዘው ሄዱ፤ ወደ በለዓምም መጡ፥ የባላቅንም ቃል ነገሩት። |
ገዥዎችሽ ዐመፀኞችና የሌባ ግብረ ዐበሮች ናቸው፤ ሁሉም ጉቦን ይወዳሉ፤ እጅ መንሻንም በብርቱ ይፈልጋሉ፤ አባት ለሌላቸው አይቆሙም፤ የመበለቶችንም አቤቱታ አይሰሙም።
መብል የሚወዱ ከቶ የማይጠግቡ ውሾች ናቸው፤ እረኞቹም ማስተዋል የማይችሉ ናቸው፤ ሁሉም ወደ መንገዳቸው ዞሩ፥ ከፊተኛው እስከ ኋለኛው ድረስ ሁሉ፥ እያንዳንዳቸው ወደ ጥቅማቸው ዘወር ብለዋል።
እፍኝ ገብስና ቁራሽ እንጀራ ለማግኘት ብላችሁ፥ ውሸት ለሚሰሙት ሕዝቤ እየዋሻችሁ፥ ሞት የማይገባቸውን ነፍሳት በመግደል፥ በሕይወትም መኖር የማይገባቸውን ነፍሳት በሕይወት በማትረፍ በሕዝቤ ፊት አርክሳችሁኛል።
የባቢሎን ንጉሥ ምዋርቱን ያምዋርት ዘንድ በመንታ መንገድ ላይ በሁለቱ መንገዶች ራስ ላይ ቆሞ ነበር፤ ፍላጾችን ወዘወዘ፥ ከተራፊምም ጠየቀ፥ ጉበትም ተመለከተ።
አለቆችዋ በጉቦ ይፈርዳሉ፥ ካህናቷ በክፍያ ያስተምራሉ፥ ነቢዮችዋ በብር ያሟርታሉ፤ “ጌታ በመካከላችን አይደለምን? ክፉ ነገር በእኛ ላይ አይመጣብንም” እያሉ በጌታ ይደገፋሉ።
በያዕቆብ ላይ አስማት የለም፥ በእስራኤልም ላይ ምዋርት የለም፤ በጊዜው ስለ ያዕቆብና ስለ እስራኤል እንዲህ ይባላል፦ ‘እግዚአብሔር ምን አደረገ!’
በለዓምም ጌታ እስራኤልን መባረክ ደስ እንደሚያሰኘው ባየ ጊዜ፥ አስቀድሞ ያደርግ የነበረውን አስማት ለመሻት አልሄደም፤ ነገር ግን ወደ ምድረ በዳ ፊቱን አቀና።
እንደ እነዚህ ያሉት ሰዎች የገዛ ሆዳቸውን እንጂ ጌታችንን ክርስቶስን አያገለግሉምና፤ በሚያሳምን ንግግርና በሽንገላ የየዋሆችን ልብ ያታልላሉ።