ዘኍል 21:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ወደ ብኤር ተጓዙ፤ ይኸውም ጌታ ሙሴን፦ “ሕዝቡን ሰብስብ ውኃንም እሰጣቸዋለሁ” ብሎ የተናገረለት ጉድጓድ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም እግዚአብሔር ለሙሴ፣ “ሰዎቹን በአንድነት ሰብስባቸውና ውሃ እሰጣቸዋለሁ” ወዳለበት ብኤር ወደተባለው የውሃ ጕድጓድ ጕዟቸውን ቀጠሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም ተነሥተው “የውሃ ጒድጓዶች” ወደ ተባለው ስፍራ ሄዱ፤ በእዚያም እግዚአብሔር ሙሴን “ሕዝቡን በአንድነት ሰብስባቸውና ውሃ እሰጣቸዋለሁ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን፥ “ሕዝቡን ሰብስብ፤ የሚጠጡት ውኃ እሰጣቸዋለሁ” ብሎ ወደ ተናገረላት ጕድጓድ ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚያም ወደ ብኤር ተጓዙ፤ ይኸውም እግዚአብሔር ሙሴን፦ ሕዝቡን ሰብስብ ውኃንም እሰጣቸዋለሁ ብሎ የተናገረለት ጕድጓድ ነው። |
እነሆ እኔ በዚያ በኮሬብ በዓለት ላይ በፊትህ እቆማለሁ፤ ዓለቱንም ትመታለህ፥ ከእርሱ ውኃ ይወጣል፥ ሕዝቡም ከእርሱ ይጠጣል አለው። ሙሴም በእስራኤል ሽማግሌዎች ፊት እንዲሁ አደረገ።
“በትሩን ውሰድ፤ አንተና ወንድምህ አሮን ማኅበሩን ሰብስቡ፥ እነርሱም ዓይናቸው እያየ ድንጋዩ ውኃን እንዲሰጥ ተናገሩት፤ ለእነርሱም ከድንጋዩ ውኃ ታወጣላቸዋለህ፤ እንዲሁም ለማኅበሩና ለከብቶቻቸው የሚጠጣ ወኃ ትሰጣቸዋለህ።”
ኢየሱስ መልሶ “የእግዚአብሔርን ስጦታና ‘ወሃ አጠጪኝ’ የሚልሽ ማን መሆኑን ብታውቂ ኖሮ፥ አንቺ በለመንሽው ነበር፤ የሕይወትም ውሃ በሰጠሽ ነበር፤” አላት።
እኔ ከምሰጠው ውሃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘለዓለም አይጠማም፤ እኔ የምሰጠው ውሃ በእርሱ ውስጥ ለዘለዓለም ሕይወት የሚፈልቅ የውሃ ምንጭ ይሆናል እንጂ፤” አላት።