ዘኍል 18:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእስራኤል ዘንድ እርም የሆነው ሁሉ ለአንተ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ለእግዚአብሔር ፈጽሞ የተሰጠ በእስራኤል ያለ ማንኛውም ነገር ሁሉ የአንተ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በእስራኤል ውስጥ ሙሉ በሙሉ ለእኔ የተለየ ነገር ሁሉ ለእናንተ ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእስራኤል ልጆች ዘንድ የተከለከለው ሁሉ ለአንተ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእስራኤል ዘንድ እርም የሆነው ሁሉ ለአንተ ይሆናል። ከሰው ወይም ከእንስሳ ቢሆን፥ |
“ነገር ግን ሰው የእርሱ ከሆነው ነገር ሁሉ ለጌታ ለይቶ እርም ያደረገው፥ ሰው ቢሆን ወይም እንስሳ ወይም የርስቱ እርሻ ቢሆን፥ አይሸጥም፥ አይቤዥም፤ እርም የሆነ ነገር ሁሉ ለጌታ እጅግ የተቀደሰ ነው።