ዘኍል 16:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም ሆነ፤ እነዚህን ቃላት ሁሉ ተናግሮ በጨረሰ ጊዜ ከበታቻቸው ያለው መሬት ተሰነጠቀ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህን ሁሉ ተናግሮ እንደ ጨረሰ የቆሙባት ምድር ተሰነጠቀች፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴ ይህን ተናግሮ እንዳበቃ፥ ዳታንና አቤሮን የቆሙበት ምድር ተከፍታ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ሆነ፤ ይህን ቃል ሁሉ መናገር በፈጸመ ጊዜ ከበታቻቸው ያለችው መሬት ተሰነጠቀች፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ሆነ፤ ይህን ቃል ሁሉ መናገር በፈጸመ ጊዜ ከበታቻቸው ያለው መሬት ተሰነጠቀ፤ |
ጌታ ግን አንድ አዲስ ነገር ቢፈጥር፥ ምድርም አፍዋን ከፍታ እነርሱን ለእነርሱም ያለውን ሁሉ ብትውጣቸው፥ በሕይወታቸውም ወደ ሲኦል ቢወርዱ፥ ያንጊዜ እነዚህ ሰዎች ጌታን እንደ ናቁ ታውቃላችሁ።”
“አባታችን በምድረ በዳ ሞተ፤ በራሱ ኃጢአት ሞተ እንጂ ቆሬን በመከተል በጌታ ላይ ከተሰበሰቡት ሰዎች መካከል አልነበረም፤ ወንዶችም ልጆች አልነበሩትም።
የሮቤል ልጅ የኤልያብ ልጆች የሆኑትን ዳታንና አቤሮንን ከነቤተሰቦቻቸው፥ ከነድንኳናቸውና ከነእንስሳታቸው በመላው እስራኤል መካከል ምድር እንዴት አፏን ከፍታ እንደዋጠቻቸው እነርሱ አላዩም።