ዘኍል 16:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከቆሬና ከዳታን ከአቤሮንም ማደሪያ ከዙሪያውም ሁሉ ርቀው ገለል አሉ፤ ዳታንና አቤሮንም ሚስቶቻቸውም ልጆቻቸውም ሕፃናቶቻቸውም ወጥተው በድንኳኖቻቸው ደጃፍ ቆሙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እነርሱ ከቆሬ፣ ከዳታንና ከአቤሮን ድንኳን ራቁ። ዳታንና አቤሮን ወጥተው ከሚስቶቻቸው፣ ከልጆቻቸውና ከሕፃናቶቻቸው ጋራ በየድንኳኖቻቸው ደጃፍ ላይ ቆመው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሕዝቡ ከቆሬ፥ ከዳታንና ከአቤሮን ድንኳኖች ፈቀቅ አሉ። ዳታንና አቤሮንም ወጥተው ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋር በድንኳናቸው ደጃፍ ቆመው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከቆሬ ድንኳን ዙሪያም ሁሉ ፈቀቅ አሉ፤ ዳታንና አቤሮንም ከሴቶቻቸው፥ ከልጆቻቸውና ከጓዛቸው ጋር ወጥተው በድንኳኖቻቸው ደጃፍ ቆሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከቆሬና ከዳታን ከአቤሮንም ማደሪያ ከዙሪያውም ሁሉ ፈቀቅ አሉ፤ ዳታንና አቤሮንም ሴቶቻቸውም ልጆቻቸውም ሕፃናቶቻቸውም ወጥተው በድንኳኖቻቸው ደጃፍ ቆሙ። |
ሙሴ ወደ ድንኳኑ በሚሄድበት ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ይነሡ ነበር፥ እያንዳንዱም በድንኳኑ ደጃፍ ይቆምና ሙሴ ወደ ድንኳኑ እስኪገባ ድረስ ይመለከቱት ነበር።