ዘኍል 14:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በቀር በእርሷ ላስቀምጣችሁ እጄን ዘርግቼ ወደ ማልሁላችሁ ምድር በእውነት እናንተ አትገቡም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መኖሪያችሁ እንድትሆን በጽኑ ወደማልሁላችሁ ምድር ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በቀር ከእናንተ አንዳችሁም አትገቡባትም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደዚያች ምድር ገብታችሁ እንደምትኖሩ ቃል ገብቼላችሁ ነበር፤ ነገር ግን ከየፉኔ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በቀር ከእናንተ አንዱ እንኳ ወደዚያች ምድር አይገባም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በቀር በእርስዋ አስቀምጣችሁ ዘንድ እጄን ዘርግቼ ወደ ማልሁላችሁ ምድር በእውነት እናንተ አትገቡም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በቀር በእርስዋ አስቀምጣችሁ ዘንድ እጄን ዘርግቼ ወደ ማልሁላችሁ ምድር በእውነት እናንተ አትገቡም። |
ለአብርሃም ለይስሐቅና ለያዕቆብ እሰጣታለሁ ብዬ እጄን ወደ አነሳሁባት ምድር አመጣችኋለሁ፤ እርሷንም ርስት አድርጌ እሰጣችኋለሁ፤ እኔ ጌታ ነኝ።’”
ከእናንተም ዘንድ ዓመፀኞችንና የበደሉኝን እለያለሁ። ከኖሩባትም ምድር አወጣቸዋለሁ፥ ወደ እስራኤል ምድር ግን አይገቡም፥ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።
ጌታ ስለ እነርሱ፦ “በእውነት በምድረ በዳ ይሞታሉ” ብሎ ተናግሮአልና። ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብ ከነዌም ልጅ ከኢያሱ በቀር ከእነርሱ አንድ ሰው እንኳ አልቀረም።
ሰማይንና በእርሱም ያሉትን፥ ምድርንና በእርሷም ያሉትን፥ ባሕርንና በእርሱም ያሉትን በፈጠረው፥ ከዘለዓለምም እስከ ዘለዓለም ድረስ ሕያው ሆኖ በሚኖረው ምሎ “ወደ ፊት አይዘገይም