ነህምያ 3:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአጠገባቸውም የኢየሩሳሌም ግዛት እኩሌታ ገዢ የሁር ልጅ ሬፋያ አደሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያ የሚቀጥለውን ክፍል የኢየሩሳሌም አውራጃ እኩሌታ ገዥ የሆነው የሑር ልጅ ረፋያ መልሶ ሠራ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእነርሱም ቀጥሎ ያለውን ክፍል የኢየሩሳሌም ወረዳ እኩሌታ ገዢ የሆነው የሑር ልጅ ረፋያ ሠራ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአጠገባቸውም የኢየሩሳሌም ግዛት እኩሌታ አለቃ የሆር ልጅ ረፋያ ሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአጠገባቸውም የኢየሩሳሌም ግዛት እኩሌታ አለቃ የሆር ልጅ ረፋያ አደሰ። |
ከእርሱም በኋላ የቤትጹር አውራጃ እኩሌታ ገዢ የሆነው የዓዝቡቅ ልጅ ነህምያ በዳዊት መቃብር ፊት ለፊት እስካለው ስፍራ፥ እስከ ተሠራው መዋኛ ስፍራና እስከ ኃያላኑ ቤት ድረስ አደሰ።