በሬን የሚያርድልኝ ሰውን እንደሚገድል ነው፤ ጠቦትንም የሚሠዋ የውሻውን አንገት እንደሚሰብር ነው፤ የእህልን ቁርባን የሚያቀርብ የእርያን ደም እንደሚያቀርብ ነው። እጣንን የሚያጥን ጣዖትን እንደሚባርክ ነው። እነዚህ የገዛ መንገዳቸውን መረጡ፤ ነፍሳቸውም በርኩሰታቸው ደስ ይላታል፤
ማቴዎስ 8:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእነርሱም ርቆ ብዙ የዓሣማ መንጋ ተሰማርቶ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእነርሱ ትንሽ ራቅ ብሎ፣ የብዙ ዐሣማ መንጋ ተሰማርቶ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእነርሱ ጥቂት ራቅ ባለ ስፍራ የብዙ ዐሣማዎች መንጋ ተሰማርቶ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእነርሱም ርቆ የብዙ እሪያ መንጋ ይሰማራ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእነርሱም ርቆ የብዙ እሪያ መንጋ ይሰማራ ነበር። |
በሬን የሚያርድልኝ ሰውን እንደሚገድል ነው፤ ጠቦትንም የሚሠዋ የውሻውን አንገት እንደሚሰብር ነው፤ የእህልን ቁርባን የሚያቀርብ የእርያን ደም እንደሚያቀርብ ነው። እጣንን የሚያጥን ጣዖትን እንደሚባርክ ነው። እነዚህ የገዛ መንገዳቸውን መረጡ፤ ነፍሳቸውም በርኩሰታቸው ደስ ይላታል፤
ዐሣማም፥ ምንም እንኳ ሰኰናው የተሰነጠቀ ቢሆንም ስለማያመሰኩህ፥ እርሱ ለእናንተ ንጹሕ አይደለም፤ የእነዚህን ሥጋ አትብሉ፤ ጥምባቸውንም አትንኩ።