ማቴዎስ 27:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም እንዳዘዘኝ ለሸክላ ሠሪው መሬት ከፈሉት።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታም ባዘዘኝ መሠረት ለሸክላ ሠሪው ቦታ ከፈሉ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌታም እንዳዘዘኝ ስለ ሸክላ ሠሪው መሬት ከፈሉት” ተብሎ በነቢዩ ዘካርያስ የተነገረው ትንቢት ተፈጸመ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታም እንዳዘዘኝ ስለ ሸክላ ሠሪ መሬት ሰጡት።” የሚል ተፈጸመ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታም እንዳዘዘኝ ስለ ሸክላ ሠሪ መሬት ሰጡት። የሚል ተፈጸመ። |
ጌታም፦ ሊከፍሉኝ የተስማሙበት ጥሩ ዋጋ በግምጃ ቤቱ ውስጥ አኑረው አለኝ። እኔም ሠላሳውን ብር ወስጄ በጌታ ቤት ባለው ግምጃ ክፍል ውስጥ አኖርኩት።