ማቴዎስ 26:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደቀ መዛሙርቱም ይህን አይተው ተቆጡና እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሁሉ ብክነት ለምንድን ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደቀ መዛሙርቱ ይህን በተመለከቱ ጊዜ ተቈጥተው እንዲህ አሉ፤ “ይህ ሁሉ ብክነት ለምንድን ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደቀ መዛሙርቱ ይህን አይተው ተቈጡና እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሽቶ ለምን በከንቱ ባከነ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደቀ መዛሙርቱም ይህን አይተው ተቈጡና “ይህ ጥፋት ለምንድር ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደቀ መዛሙርቱም ይህን አይተው ተቍኦጡና፦ ይህ ጥፋት ለምንድር ነው? |
ደግሞም የሰውን ድካምና የብልሃት ሥራውን ሁሉ ተመለከትሁ፥ በባልንጀራም ዘንድ ቅንዓት እንደሚያስነሣ አየሁ፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።
እናንተ እንዲህ ትላላችሁ፦ “እህልን እንድንሸጥ መባቻው መቼ ያልፋል? ስንዴውንም ለሽያጭ ገበያ ለማቅረብ ሰንበት መቼ ያበቃል? የኢፍ መስፈሪያውንም እናሳንሳለን፥ ሰቅሉንም እናበዛለን፥ በሐሰተኛም ሚዛን እናታልላለን፥
“እነሆ፥ ይህ ድካም ነው ብላችሁ ጢቅ አላችሁበት፥” ይላል የሠራዊት ጌታ፤ “የተሰረቀውን፥ አንካሳውንና የታመመውን አምጥታችኋል፤ እንዲሁም ቁርባንን አምጥታችኋል፤ በውኑ ከእጃችሁ መቀበል ይገባኛልን?” ይላል ጌታ።
በማዕድም ተቀምጦ ሳለ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ የበዛ ሽቶ የሞላበት የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ ወደ እርሱ ቀረበች፤ በራሱ ላይም አፈሰሰችው።