ጌታም እንዲህ አለኝ፦ “ነቢያቱ በስሜ የውሸትን ትንቢት ይናገራሉ፤ አላክኋቸውም፥ አላዘዝኋቸውም፥ አልተናገርኋቸውም፤ የውሸትን ራእይ ምዋርትንም ከንቱንም ነገር የልባቸውንም ሽንገላ ይሰብኩላችኋል።
ማቴዎስ 24:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብዙዎች ‘መሢሑ እኔ ነኝ’ እያሉ በስሜ ይመጣሉና ብዙዎችንም ያስታሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብዙዎች፣ ‘እኔ ክርስቶስ ነኝ’ በማለት በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብዙዎች ‘እኔ መሲሕ ነኝ!’ እያሉ በስሜ ይመጣሉ፤ ብዙ ሰዎችንም ያሳስታሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብዙዎች ‘እኔ ክርስቶስ ነኝ፤’ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብዙዎች፦ እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ። |
ጌታም እንዲህ አለኝ፦ “ነቢያቱ በስሜ የውሸትን ትንቢት ይናገራሉ፤ አላክኋቸውም፥ አላዘዝኋቸውም፥ አልተናገርኋቸውም፤ የውሸትን ራእይ ምዋርትንም ከንቱንም ነገር የልባቸውንም ሽንገላ ይሰብኩላችኋል።
ስለዚህም ኢየሱስ “የሰውን ልጅ ከፍ ከፍ ባደረጋችሁት ጊዜ እኔ እንደሆንሁ፥ እንደዚህም የምናገረው አባቴ እንዳስተማረኝ እንጂ በእራሴ ምንም እንደማላደርግ በዚያን ጊዜ ታውቃላችሁ።
ልጆች ሆይ፥ ይህ የመጨረሻው ሰዓት ነው፤ የክርስቶስ ተቃዋሚ ይመጣል ሲባል እንደ ሰማችሁት አሁን እንኳ ብዙ የክርስቶስ ተቃዋሚዎች መጥተዋል፤ በዚህም ይህ የመጨረሻው ሰዓት እንደሆነ እናውቃለን።
ኢየሱስ ክርስቶስም በሥጋ እንደመጣ የማያምን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም፤ ይህም ይመጣል ሲባል የሰማችሁት የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ ነው፥ አሁንም እንኳ በዓለም ውስጥ አለ።