ማቴዎስ 14:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደቀመዛሙርቱ በባሕር ላይ ሲሄድ ባዩት ጊዜ “ምትሐት ነው” ብለው ደነገጡ፤ ከፍርሃትም የተነሣ ጮኹ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደቀ መዛሙርቱም በባሕሩ ላይ ሲራመድ ባዩት ጊዜ ፈሩ፤ እነርሱም፣ “ምትሀት ነው!” በማለት በፍርሀት ጮኹ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደቀ መዛሙርቱም በባሕሩ ላይ እየተራመደ ሲሄድ ባዩት ጊዜ በጣም ፈርተው ደነገጡ፤ “ይህ ምትሐት ነው!” ብለውም በፍርሃት ጮኹ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደቀ መዛሙርቱም በባሕር ላይ ሲሄድ ባዩት ጊዜ “ምትሐት ነው” ብለው ታወኩ፤ በፍርሃትም ጮኹ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደቀ መዛሙርቱም በባሕር ላይ ሲሄድ ባዩት ጊዜ፦ ምትሐት ነው ብለው ታወኩ በፍርሃትም ጮኹ። |
ፈርተውም ፊታቸውን ወደ ምድር አቀርቅረው ሳሉ፥ እንዲህ አሉአቸው “ሕያዉን ለምን በሙታን መካከል ትፈልጉታላችሁ? እርሱ እዚህ የለም፤ ይልቁንም ተነሥቶአል።