ማቴዎስ 10:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁለት ድንቢጦች በአምስት ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ከእነርሱ አንዲትዋ እንኳ ያለ አባታችሁ ፈቃድ በምድር ላይ አትወድቅም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአንድ ሳንቲም ከሚሸጡት ሁለት ድንቢጦች አንዲቷ እንኳ ያለ አባታችሁ ፈቃድ ምድር ላይ አትወድቅም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁለት ድንቢጦች በአምስት ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ይሁን እንጂ፥ የሰማይ አባታችሁ ሳይፈቅድ፥ አንዲቱ ድንቢጥ እንኳ በምድር ላይ ወድቃ አትቀርም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁለት ድንቢጦች በአምስት ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ከእነርሱም አንዲቱ ያለ አባታችሁ ፈቃድ በምድር ላይ አትወድቅም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁለት ድንቢጦች በአምስት ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ከእነርሱም አንዲቱ ያለ አባታችሁ ፈቃድ በምድር ላይ አትወድቅም። |
ወደ ሰማይ ወፎች ተመልከቱ፤ አይዘሩም፥ ወይም አያጭዱም፥ ወደ ጎተራም አይሰበስቡም፤ ነገር ግን የሰማዩ አባታችሁ ይመግባቸዋል፤ ታዲያ እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን?