ማርቆስ 8:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም፥ “ስንት እንጀራ አላችሁ?” ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም፥ “ሰባት” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም፣ “ስንት እንጀራ አላችሁ?” ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም፣ “ሰባት” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስም “ስንት እንጀራ አላችሁ?” ብሎ ጠየቃቸው፤ እነርሱም “ሰባት እንጀራ አለን፤” አሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም “ስንት እንጀራ አላችሁ?” ብሎ ጠየቃቸው፤ እነርሱም “ሰባት” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ ስንት እንጀራ አላችሁ? ብሎ ጠየቃቸው፥ እነርሱም፦ ሰባት አሉት። |
እርሱም፥ መሬት ላይ እንዲቀመጡ ሕዝቡን አዘዘ፤ ሰባቱን እንጀራ ይዞ ካመሰገነ በኋላ ቆርሶ ለሰዎቹ እንዲያድሉ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው፤ እነርሱም ለሕዝቡ አደሉት።
እርሱ ግን፦ “እናንተ የሚበሉትን ስጡአቸው፤” አላቸው። እነርሱም፦ “ሄደን ለዚህ ሁሉ ሕዝብ ምግብ ካልገዛን በቀር ከአምስት እንጀራና ከሁለት ዓሣ የሚበልጥ የለንም፤” አሉት፤