ዮናዳብም፥ “እንግዲያው የታመምህ መስለህ አልጋ ላይ ተኛ፤ አባትህ ሊጠይቅህ ሲመጣም፥ ‘እኅቴ ትዕማር መጥታ የምበላውን ነገር ትስጠኝ፤ እዚህ በአጠገቤ እያየኋት ምግብ አዘጋጅታ እርሷ ራስዋ እንድታጐርሰኝ እፈልጋለሁ’ በለው” አለው።
ማርቆስ 6:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷም ወጥታ እናቷን፥ “ምን ልለምነው?” አለቻት። እናቷም፥ “የመጥምቁን የዮሐንስን ራስ” አለቻት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷም ወጥታ እናቷን፣ “ምን ልለምነው?” አለቻት። እናቷም፣ “የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ” አለቻት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋም ወደ እናትዋ ሄዳ፥ “ምን ልጠይቅ?” አለቻት፤ እናትዋም “ ‘የመጥምቁ ዮሐንስ ራስ ይሰጠኝ፤’ ብለሽ ጠይቂ፤” አለቻት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወጥታም ለእናትዋ “ምን ልለምነው?” አለች። እርስዋም “የመጥምቁን የዮሐንስን ራስ” አለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወጥታም ለእናትዋ፦ ምን ልለምነው? አለች። እርስዋም፦ የመጥምቁን የዮሐንስን ራስ አለች። |
ዮናዳብም፥ “እንግዲያው የታመምህ መስለህ አልጋ ላይ ተኛ፤ አባትህ ሊጠይቅህ ሲመጣም፥ ‘እኅቴ ትዕማር መጥታ የምበላውን ነገር ትስጠኝ፤ እዚህ በአጠገቤ እያየኋት ምግብ አዘጋጅታ እርሷ ራስዋ እንድታጐርሰኝ እፈልጋለሁ’ በለው” አለው።