ማርቆስ 5:41 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም የልጅቱን እጅ ይዞ፥ “ጣሊታ ቁሚ” አላት፤ ትርጉሙም፥ “አንቺ ልጅ ተነሺ” ማለት ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የብላቴናዪቱን እጅ ይዞ፣ “ጣሊታ ቁሚ!” አላት፤ ትርጕሙም፣ “አንቺ ልጅ ተነሺ” ማለት ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የልጅትዋንም እጅ ይዞ፥ “ጣሊታ ቁሚ!” አላት፤ ትርጒሙም “አንቺ ልጅ ተነሺ እልሻለሁ፤” ማለት ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የብላቴናይቱንም እጅ ይዞ “ጣሊታ ቁሚ!” አላት፤ ፍችውም “አንቺ ብላቴና ተነሽ እልሻለሁ!” ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የብላቴናይቱንም እጅ ይዞ፦ ጣሊታ ቁሚ አላት፤ ፍችውም አንቺ ብላቴና ተነሽ እልሻለሁ ነው። |
“የብዙ ሕዝቦች አባት አድርጌሃለሁ” ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ የሞተውን ሕያው በሚያደርግ የሌለውንም እንዳለ አድርጎ በሚጠራ ባመነበት አምላክ ፊት ነው።