ማርቆስ 5:38 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ምኵራቡ አለቃ ቤት በደረሱ ጊዜ፥ ሲታወኩ፥ ሰዎቹም ሲያለቅሱና አምርረውም ሲጮኹ ተመለከተ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ምኵራቡ አለቃ ቤት እንደ ደረሱ፣ ኢየሱስ ግርግሩንና ሰዎቹም ዋይ ዋይ እያሉ አምርረው ሲያለቅሱ ተመለከተ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ምኲራብ አለቃው ቤት በደረሱ ጊዜ ኢየሱስ ሰዎቹ ሲንጫጩና ሲያለቅሱ፥ ሲጮኹም ተመለከተ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ምኵራቡ አለቃ ቤትም መጥቶ ሰዎች ሲንጫጩና ሲያለቅሱ ዋይታም ሲያበዙ አየ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ምኵራቡ አለቃ ቤትም መጥቶ ሰዎች ሲንጫጩና ሲያለቅሱ ዋይታም ሲያበዙ አየ፤ |
ይህንም ሲነግራቸው ሳለ እነሆ አንድ ገዢ መጥቶ እየሰገደ “ልጄ አሁን ሞተች፤ ነገር ግን መጥተህ እጅህን ጫንባት፥ በሕይወትም ትኖራለች፤” አለው።
ጴጥሮስም ተነሥቶ ከእነርሱ ጋር መጣ፤ በደረሰም ጊዜ በሰገነት አወጡት፤ መበለቶችም ሁሉ እያለቀሱ ዶርቃ ከእነርሱ ጋር ሳለች ያደረገቻቸውን ቀሚሶችንና ልብሶችን ሁሉ እያሳዩት በፊቱ ቆሙ።