ማርቆስ 2:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞ “ሰንበት ስለ ሰው ተፈጥሯል እንጂ ሰው ስለ ሰንበት አልተፈጠረም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም እንዲህ አላቸው፤ “ሰንበት ለሰው ተፈጠረ እንጂ፣ ሰው ለሰንበት አልተፈጠረም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደግሞም ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “ሰንበት ለሰው ተሠራ እንጂ ሰው ለሰንበት አልተፈጠረም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞ “ሰንበት ስለ ሰው ተፈጥሮአል እንጂ ሰው ስለ ሰንበት አልተፈጠረም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞ፦ ሰንበት ስለ ሰው ተፈጥሮአል እንጂ ሰው ስለ ሰንበት አልተፈጠረም፤ |
ፈቃድህን በተቀደሰው ቀኔ ከማድረግ፥ እግርህን ወደ ሰንበት፥ ሰንበትንም ደስታ፥ ጌታንም የቀደሰውን ክቡር ብትለው፥ በራስህ መንገድህን ከመጓዝ፥ ፈቅድህንም ከመፈጸም፥ ከንቱ ነገርንም ከመናገር ተከልክለህ ብታከብረው፥
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “እስቲ ልጠይቃችሁ፤ በሰንበት ቀን የተፈቀደው በጎ ማድረግ ነውን ወይንስ ክፉ? ነፍስ ማዳን ነውን ወይንስ ማጥፋት?”
ሰባተኛው ቀን ግን ለጌታ አምላካችሁ ሰንበት ነው፥ አንተ ወንድ ልጅህም ሴት ልጅህም አገልጋይህም፥ አገልጋይትህም፥ በሬህም፥ አህያህም፥ ከብትህም ሁሉ፥ ወይም በደጆችህም ውስጥ ያለ እንግዳ፥ በእርሱ ምንም ሥራ አትሥሩ፥ አንተ እንደምታርፍ ሁሉ አገልጋይህና አገልጋይትህ እንዲያርፉ።