በአረጀ አቁማዳም አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን፥ የወይን ጠጁ አቁማዳውን ያፈነዳል፤ የወይኑም ጠጅ ይፈሳል፤ አቁማዳውም ይጠፋል፤ አዲሱን የወይን ጠጅ ግን በአዲስ አቁማዳ ያኖራሉ።”
ማርቆስ 2:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሰንበትም በእርሻ መካከል ሲያልፍ ደቀመዛሙርቱ እየሄዱ እሸት ይቀጥፉ ጀመር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሰንበት ቀን ኢየሱስ በዕርሻ መካከል ሲያልፍ፣ ዐብረውት በመጓዝ ላይ የነበሩት ደቀ መዛሙርቱ እሸት ይቀጥፉ ጀመር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሰንበት ቀን ኢየሱስ በስንዴ እርሻ መካከል ያልፍ ነበር። ደቀ መዛሙርቱ ሲሄዱ የስንዴ እሸት መቅጠፍ ጀመሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሰንበትም በእርሻ መካከል ሲያልፍ ደቀ መዛሙርቱ እየሄዱ እሸት ይቀጥፉ ጀመር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሰንበትም በእርሻ መካከል ሲያልፍ ደቀ መዛሙርቱ እየሄዱ እሸት ይቀጥፉ ጀመር። |
በአረጀ አቁማዳም አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን፥ የወይን ጠጁ አቁማዳውን ያፈነዳል፤ የወይኑም ጠጅ ይፈሳል፤ አቁማዳውም ይጠፋል፤ አዲሱን የወይን ጠጅ ግን በአዲስ አቁማዳ ያኖራሉ።”