ማርቆስ 2:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሲያልፍም በመቅረጫው ተቀምጦ የነበረውን የእልፍዮስን ልጅ ሌዊን አየና “ተከተለኝ፤” አለው። ተነሥቶም ተከተለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያም ሲያልፍ የእልፍዮስን ልጅ ሌዊን በቀረጥ መሰብሰቢያው ስፍራ ተቀምጦ አየውና፣ “ተከተለኝ” አለው፤ እርሱም ተነሥቶ ተከተለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም ሲያልፍ ሳለ በቀረጥ መቀበያ ስፍራ ተቀምጦ የነበረውን የእልፍዮስን ልጅ ሌዊን አይቶ፥ “ተከተለኝ” አለው፤ እርሱም ተነሥቶ ተከተለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሲያልፍም በመቅረጫው ተቀምጦ የነበረውን የእልፍዮስን ልጅ ሌዊን አየና “ተከተለኝ፤” አለው። ተነሥቶም ተከተለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሲያልፍም በመቅረጫው ተቀምጦ የነበረውን የእልፍዮስን ልጅ ሌዊን አየና፦ ተከተለኝ አለው። ተነሥቶም ተከተለው። |
በገቡም ጊዜ ወደሚኖሩበት ሰገነት ወጡ፤ ጴጥሮስና ዮሐንስም፥ ያዕቆብም፥ እንድርያስም፥ ፊልጶስም፥ ቶማስም፥ በርተሎሜዎስም፥ ማቴዎስም፥ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብም፥ ቀናተኛ የሚባለው ስምዖንም፥ የያዕቆብ ልጅ ይሁዳም።