ሉቃስ 8:55 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መንፈሷም ተመለሰች፤ ፈጥናም ተነሣች፤ የምትበላውም ነገር እንዲሰጣት አዘዘ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የልጅቷም መንፈስ ተመለሰ፤ ወዲያውም ተነሥታ ቆመች፤ ኢየሱስም የሚበላ ነገር እንዲሰጧት አዘዛቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋም ነፍስዋ ስለ ተመለሰችላት ወዲያውኑ ብድግ አለች፤ ኢየሱስም “የምትበላውን ስጡአት!” ሲል አዘዘ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወዲያውም ነፍስዋ ተመልሶላት ፈጥና ቆመች፥ የምትበላውንም ይሰጡአት ዘንድ አዘዘ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነፍስዋም ተመለሰች፥ ፈጥናም ቆመች፥ የምትበላውንም እንዲሰጡአት አዘዘ። |
ሞቶ የነበረውም ሰው እጆቹና እግሮቹ እንደ ተገነዙ ወጣ፤ ፈቱም በጨርቅ እንደ ተጠመጠመ ነበረ። ኢየሱስም “ፍቱትና ይሂድ፤ ተዉት፤” አላቸው።